በዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዳያስፖራ አማካሪዋ ለአህጉሪቱ ያላቸውን ትኩረት ይናገራሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል፣ በአፍሪካ የዲያስፖራ ተሳትፎ አማካሪ የሚኾኑ 12 የምክር ቤት አባላትን ስም ዝርዝር፣ በዚኽ ሳምንት መግቢያ ላይ ይፋ አድርገዋል። ከእኒኽም አንዷ የካሊፎርኒያ ግዛት ነዋሪዋ ትውልደ ኤርትራዊቷ ወሮ. አልማዝ ነጋሽ ናቸው። ወሮ. አልማዝ፣ በዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዳያስፖራ የትስስር መድረክ መሥራች ናቸው።

ተቋሙ፣ ላለፉት 13 ዓመታት፣ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉ አፍሪካውያን፥ በልዩ ልዩ የአፍሪካ ሀገራት ሙዓለ ነዋይ እንዲያፈሱ፣ በንግድ ዙሪያ እንዲወያዩና በአህጉሪቱ የሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች የሥልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ሲደርግ ቆይቷል።

ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ ያደረጉት ወሮ. አልማዝ፣ ተቋማቸው ስለሚሠራቸው ሥራዎች እና ዐዲስ በተመረጡበት ኮሚቴ አማካይነት፣ በአፍሪካ ትኩረት እንዲሰጣቸው ስለሚያስቧቸው ጉዳዮች አንሥተዋል።

ያነጋገረቻቸው ኤደን ገረመው ናት። ቆይታቸው ቀጥሎ ይቀርባል።