የጽኑ ኩላሊት ሕመም መንሥኤዎች ምንድን ናቸው?

Your browser doesn’t support HTML5

በተለምዶ ሰዎች፥ ሁለት ኩላሊቶችን ይዘው ቢወለዱም፣ በአንድ ኩላሊትም መኖር እንደሚችሉ፣የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ኩላሊት፣ በደም ውስጥ ያሉ መርዛማ/መራዥ/ ነገሮችን የማጽዳት ሥራ አለው፡፡ የኩላሊት ሕመም፣ ኩላሊት ጉዳት ሲደርስበትና ደም የማጣራት መደበኛ ተግባሩ ሲስተጓጎል የሚከሠት ነው፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት፣ የኩላሊት ሕመም ጫና፣ በአዳጊ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ላይ ከፍተኛ እንደኾነ አስታውቋል፡፡
በዓለም ላይ፣ 850 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች የኩላሊት ሕመም አለባቸው፡፡ ከእኒኽም መካከል፣ በየዓመቱ 2.6 ሚሊዮን የሚኾኑት፣ ከበሽታው የተነሳ ለኅልፈተ ሕይወት እንደሚዳረጉ፣ የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡