ትኩረት የተነፈገው የሴት ልጅ ግርዛት

Your browser doesn’t support HTML5

እንኳን ለአለም የሴቶች ቀን አደረሳቹ፡፡ የዚህ ዓመት የሴቶች ቀን መሪ ቃል 'አካታችነትን ማነቃቃት' ይላል። በዛሬው ኑሮ በጤንነት በአለም ላይ ትኩረት የተነፈገው ነገር ግን አሁንም ድረስ የብዙ ልጃገረዶች የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በሚያሳድረው የሴት ልጅ ግርዛት ላይ ያተኩራል፡፡

የሴት ልጅ ግርዛት በአለም ዙሪያ አሁንም ድረስ በልጃገረድ እና ህጻናት ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለ አጉል ልማድ ነው። የመንግስታቱ ድርጅት የህጻናት ፈንድ ዩኒሴፍ በአለም ላይ 200 ሚሊየን የሚሆኑ ሴቶች ከአራቱ የግርዛት ዓይነቶች አንደኛው ተፈጽሞባቸዋል ሲል አስታውቋል። የአለም የጤና ድርጅት በሴት ልጅ ላይ የሚፈጸም ግርዛት ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ፣ የሰውነት መቆጣት በማስከተል እንዲሁም ደግሞ ሴቲቷ እድሜዋ ለአቅመ ወሊድ ደርሶ በምታምጥበት ወቅት አስከፊ ስቃይ በማስከተል እና ለተለያዩ የአዕምሮ ጠባሳዎች ይዳርጋታል ሲል አስታውቋል። በተጨማሪም ድርጅቱ በየዓመቱ ሶስት ሚሊየን የሚሆኑ ሴቶች በአፍሪካ ይገረዛሉ ሲል አስታውቋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/