የደራሲና ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን አለም አቀፍ ሬስቶራንቶች

Your browser doesn’t support HTML5

ትውልደ ኢትዮጵያዊው አለም አቀፍ የምግብ አብሳይ ማርከሰ ሳሙኤልሰን ገና በለጋነቱ እናቱን በቲቢ በሽታ አጥቷል። በኋላም በጉዲፈቻ ተወስዶ በስዊዲን አድጓል። ማርከስ ከአስር በላይ መጽሃፍትን ጽፎ ያሳተመ፣ የተለያዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ የሚሳተፍ ሲሆን፣ በትላልቅ ዩኒቨስቲዎች ምግብ ሙያ በማስተማር ዝነኝነትን አትርፏል።

በኦባማ አስተዳደር ለከፍተኛ ባለስልጣናት በተዘጋጁ ግብዣዎች ላይ ምግብ ከማብሰል ባለፈ፤ በአሁን ሰዓት በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ አስር ምግብ ቤቶች ባለቤትም ነው።