"አካል ጉዳተኛ ሴቶች ይችላሉ ብለን ስንወጣ እጣቢ ተደፍቶብን ያውቃል" ወ/ሮ ሂዳያ አሊ

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በዛሬው ዕለት “የዛሬው የሰረአተ ፆታ እኩልነት ለዘላቂ ሕይወት” በሚል ቃል በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል፡፡ ቀኑን ታሳቢ በማድረግ በሃረሪ ክልል የሴት አካል ጉዳተኞች ማኅበር መስራች የሆኑ ሁለት አካል ጉዳተኛ የመብት ተሟጋቾችን ጋብዘናል፡፡ ወ/ሮ ሂዳያ አሊ እና ወ/ሮ አዜብ ሺፈራው የሃረሪ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ለትምህርት ለሥራ እንዲወጡ በማኅበራቸው አማካኝነት ራሳቸው ተምሳሌት አድርገው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ማኅበረሰቡን ለማስተማር ስንወጣ ቆሻሻ እጣቢ እስከመደፋት ደርሶብን ያውቃል ይላሉ፡፡ ሙሉ ቆይታውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡