በክር መነደፍ - ቆይታ ከሠዓሊ እና ዲዛይነር ፍቅር ሰሎሞን ጋራ

Your browser doesn’t support HTML5

ፍቅር ሰሎሞን፣ ፍቅር ጨርቃጨርቅ እና የሸራ ላይ የሥዕል ጥበብን አንድ ላይ በማዋሐድ ለየት ባለ መልኩ ሥራዎቿን የምታቀርብ ወጣት ሠዓሊ ናት። በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብ መምህርት የኾኑት እናቷ እና በተመሳሳይ ሞያ ውስጥ የሚገኘው ታላቅ ወንድሟ፣ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳሳደሩባት ፍቅር ትናገራለች።

ፍቅር ሰሎሞን፣ ከዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ “አለ” የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት፣ በጨርቃጨርቅ ዲዛይን የተመረቀች ሲኾን፤ ‘ጆንያ’ በተሰኘ የንግድ መለዮ፣ የሴት ቦርሳዎችንና ስካርፎችን ዲዛይን ታደርጋለች።

አብዛኛውን ጊዜ ሥራዎቿ፣ ያለእርሷ ፈቃድ በገበያ ላይ ኮፒ መደረጋቸውን የገለጸችው ፍቅር፣ የአእምሮ ሥራዎች መብት ጥበቃ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ታሳስባለች።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/