“ተስፋ ከቤት ወዲያ” በ“ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን”

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቀን፣ በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም፣ “ተስፋ ከቤት ወዲያ” በሚል መሪ ቃል በመታሰብ ላይ ይገኛል። የመንግሥታቱ ድርጅት፣ በአሁን ሰዓት በዓለም ዙሪያ፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሰዎች፣ ከመኖሪያ ቀዬአቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው እንደሚገኙ በቅርቡ አስታውቋል። ስደተኞች እና ቤተ ሰዎቻቸው ምቹ ወደኾኑ መኖሪያዎች እስኪዘዋወሩ ድረስ፣ እጅግ ብዙ ችግሮችን ይጋፈጣሉ። ጁሊያ ዴንግ፣ ከሰባት ዓመታት በፊት በደቡብ ሱዳን የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት በመሸሽ፣ ከሦስት ልጆቿ ጋራ ወደ ኢትዮጵያ ተሰድዳለች። ይህቺ እናት፣ አሶሳ በሚገኘው ጾሬ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ፣ ከሦስት ልጆቿ እና ከእህቷ ጋራ ለአምስት ዓመታት ኖራለች።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/