በዲላ ዩንቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ሁለገብ እንዲሆኑ እያገዘ ያለው የዜሮ ፕላን እንቅስቃሴ

Your browser doesn’t support HTML5

ወጣቶች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ከትምህርት ውጪ ለሌሎች ችግሮቻቸው ግን መፍትሄ የሚያገኙበት መንገድ አልተቀየስም፡፡ በተለይም ከስነ ተዋልዶ ጋር ተያይዞ ጥንቃቄ በጎደለው ግንኙነት የተነሳ ሴት ተማሪዎች ለብዙ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡ ዲኬቲ ኢትዮጵያ በዲላ ዩኒቨርስቲ ዜሮ ፕላን የተሰኘ ሴት ተማሪዎች ስለ ስነ ተዋልዶ የሚያወሩበት፣ ስለሕይወት ክህሎት የሚማሩበት እና ስለወደፊቱ የሚያቅዱበትን ክበብ በመፍጠር እጅግ ስኬታማ የሆነ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል፡፡