የደረሰች ነፍሰ ጡር የሚያስመስለው ፋይብሮድ የማህጸን ዕጢ ምንድነው?
Your browser doesn’t support HTML5
በእንግሊዝኛው ሥያሜው ፋይብሮይድ የሚባለው የማኅጸን ዕጢ በምን ምክንያት እንደሚከሰት የማይታወቅ እና ለህይወት የማያሰጋ ቢሆንም፤ በሴት ልጅ አኗኗርና ልጅ የመውለድ ዕድል ላይ የሚደቅነው ችግር ሊኖር ይችላል።
በኢትዮጵያ አንዳንድ ሴቶች ስለዚህን መሰሉ የማህጸን ዕጢ ብዙም ሳያውቁ ከዘጠኝ ወር በላይ ያረገዙ መስሏቸው የተሳሳተ ግንዛቤ የሚያሳድሩበት አጋጣሚ መኖሩን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የጽንስ እና የማህጸን ህክምና ሃኪም ዶ/ር አህመድ አደም ይናገራሉ።