የአሜሪካ ቀጣሪዎች  በሃያዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያሉ ወጣቶችን መቅጠር አይፈልጉም ተባለ 

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የተሰራ አንድ አዲስ ጥናት 40 በመቶ የሚሆኑ ስራ ቀጣሪዎች እድሜያቸው በ20ዎቹ የሚገኙ ወጣቶችን ለመቅጠር እንደማይሹ ጠቆመ። በቅርቡ ይፋ የተደረገው ይኸው ጥናት አብዛኞቹ ቀጣሪዎች እድሜያቸው  በአስራዎቹ ማብቂያ እና በሃያዎቹ ውስጥ የሚገኙ  በምህጻር ‘ጄን ዚ’  የሚባሉትን አዲስ ተመራቂ  ወጣቶችን ለመቅጠር ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ነው ያመላከተው። 

ጥናቱ 800 የሚሆኑ የድርጅቶች ስራ አስኪያጆች እና ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ላይ የተደረገ ሲሆን፤ ከ 10 ቀጣሪዎች መካከል አራቱ የቅርብ ጊዜ ተመራቂዎች “ሃላፊነት የማይሰማቸው እና ለስራ ብቁ አይደሉም" ብለው ስለሚያምኑ እንደማይቀጥሯቸው ተገልጿል። ኤደን ገረመው የዶራ ሜካወርን ዘገባ እንደሚከተለው አሰናድታዋለች።