“የእናቶች ምርጥ መጽሐፍ” አሸናፊ ደራሲ ማክዳ አርሺ 

Your browser doesn’t support HTML5

ደራሲ እና ነርስ ማክዳ አርሺ፣ የሦስት ሴቶች ልጆች እናት ናት፡፡ ማክዳ፥ “The world need uniquely happy you” የተሰኘ የልጆች መጽሐፍ አሳትማለች፡፡  መጽሐፉ በይዘቱ፣ ሁሉም ሰው የራሱን ባህል እና ማንነት እንዲያከብር ያበረታታል፡፡ መጽሐፉ፣ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የብሔራዊ “የእናቶች የመጽሐፍ ምርጫ”(Mom’s choice Awards) በመባል አሸናፊ ኾኗል፡፡ “የዓለም መብራቶች” በሚል ርእስም፣ ወደ ዐማርኛ ቋንቋ ተመልሷል።

ደራሲዋ ማክዳ አርሺ፣ መጽሐፉ፣ ከዐማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ፣ ወደ ሌሎችም የአገሪቱ ቋንቋዎች እንዲተረጎም እየሠራች እንደኾነ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቃለች፡፡ ማክዳ ከኤደን ገረመው ጋራ ቆይታ አድርጋለች፡፡