ወጣቶች በውሳኔ ሰጪ ተቋማት ውስጥ እንዴት መሳተፍ ይችላሉ?  

Your browser doesn’t support HTML5

ከዐዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተግባራዊ(አፕላይድ) ሳይንስ የተመረቀችው ሜሮን አንተነህ፤ በአሁን ሰዓት የኮሙኒኬሽን አማካሪ ኾና ከተለያዩ ተቋማት ጋራ እየሠራች ትገኛለች፡፡ ሜሮን፣ ከመደበኛ ሥራዋ ጋራ፣ በአውሮፓ ኅብረት የወጣቶች እንቅስቃሴ መሥራች እና አገናኝ ኾና በበጎ ፈቃደኝነት ታገለግላለች፡፡ ወጣቶች ይህን መሰል ዕድሎችን እንዴት ማግኘት ይችላሉ? የሚያነሧቸው ጥያቄዎችስ ምንድን ናቸው? በሚሉ ጥያቄዎች ላይ፣ ከጋቢና ቪኦኤ ጋራ ቆይታ አድርጋለች።