የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እና በግጭቱ ክልሎች ያሉ ወጣቶች አስተያየት 

Your browser doesn’t support HTML5

ከአንድ ዓመት በፊት በፕሪቶሪያ የተደረገው ግጭቱን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት  እጅግ ብዙ ክፍተቶች እንዳሉበት ቢገለጽም፣ ጦርነቱ ሲካሔድ በቆየባቸው አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ አስችሏል። በጦርነቱ ተሳታፊ በነበሩት በትግራይ፣ በዐማራ እና በአፋር ክልሎች ያሉ ወጣቶች፣ በሰላም ስምምነቱ አስፈላጊነት ላይ ይስማማሉ። ይኹን እንጂ፣ በፕሪቶርያው ስምምነት ላይ የተለያዩ አቋሞች እንዳሏቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡:

በተያያዘ፣ ያለፈው አንድ ዓመት፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ኹኔታ፣ በወጣቶች ሥነ ልቡና ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳስከተለ ጥናቶች ማመላከታቸውን፣ በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ክፍል ባልደረባ ዶር. አወቀ ምሕረቱ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡

ከሽግግር ፍትሕ ጋራ በተያያዘም አስተያየታቸውንየሰጡት ዶር. አወቀ፣ በፍርድ ቤት ሒደት ላይ ብቻ ያተኮረ ፍትሕ፣ የበዳይንም ኾነ የተበዳይን የሥነ ልቡና ቁስል እንደማያሽር ገልጸው፣ ማኅበረሰብ ተኮር የእርቅ እና የውይይት መድረኮችን አስፈላጊነት አመልክተዋል።

ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።