የኢትዮጵያዊያን ሴቶችን የጤና መረጃ ክፍተት ለመሙላት ያለመው የኔ ሄልዝ

Your browser doesn’t support HTML5

ገና በሁለት ዓመት እድሜዋ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመጓዝ በዛ ያደገችው ቅድስት ተስፋዬ እድገቷ በሚኒሶታ ግዛት ነው። የመጀመሪያ ዲግሪዋን የማኅበረሰብ ጤና ሳይንስ ያጠናች ሲሆን ሁለተኛ ዲግሪዋም የሕክምና ሳይንስ ትምህርት አሰጣጥ ላይ አድርጋለች። ቅድስት የኔ ሄልዝ የተሰኘ ሴቶች ከስነ ተዋልዶ ጋር የተያያዙ እውቀቶችን የሚገበዩበት፣ የወሊድ መከላከያ መድሃኒቶችን የሚያገኙበት እና በተጨማሪም ከህክምና ባለሞያዎች ጋር የሚወያዩበት የስልክ መተግበሪያ አሰናድታለች።