ሴትነትና አካል ጉዳት ያልበገራቸው የምክር ቤት አባል ሊዲያ አሰፋ ዳውሰን

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ ዋሺንግተን ግዛት ኪንግ ካውንቲ፤ የፌደራል ዌይ ከተማን ከጎርጎርሳዊያኑ 2014 አንስቶ በምክር ቤት አባልነት በማገልግል ላይ የሚገኙት ወ/ሮ ሊዲያ አሰፋ ዳውሰን ከሰሞኑ ሲያደርጉት የነበረውን የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን በአሸናፊነት አጠናቀዋል፡፡ የሦስት ወንድ ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ሊዲያ ልጆቻቸው እራሳቸውን እስኪችሉ ጥብቀው ወደ አስተዳደር ስራ ፊታቸውን ማዞራቸውን ይገልጻሉ፡፡

በዋናነትም ስደተኛው ማኅበረሰብ ውክልና እንዲኖረው በዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ ሰጭነት ላይ የይገባኛል ስሜት በማዳበር እንዲሳተፍ ይመክራሉ፡፡ ኤደን ገረመው ከወ/ሮ ሊዲያ አሰፋ ጋር ቆይታ አድርጋ ዘገባ አሰናድታለች።