ከኻርቱም መውጣት የተሳናቸው ስደተኞች ዓለም አቀፍ ተቋማትን እየተማፀኑ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በሱዳን የጦር ኃይል እና በፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ልዩ ኃይል መካከል የሚደረገውን ውጊያ ሸሽተው የሚወጡ ስደተኞች፣ ከካርቱም ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ለመድረስ፣ 150ሺሕ የሱዳን ፓውንድ ወይም እስከ 14 ሺሕ የኢትዮጵያ ብር እንደሚጠየቁ ገለጹ። ገንዘቡን ከፍለው መውጣት ያልቻሉ ስደተኞችንም፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲታደጓቸው ጠይቀዋል።