በካታር ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቀው ሠዓሊ  

Your browser doesn’t support HTML5

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ ፈለገ ሰላም የሥነጥበብ ትምህርት ቤት የተመረቀው ሠዓሊ ተሰማ ተምትሜ ያለፉት 15 ዓመታትን ነዋሪነቱን በመካከለኛው ምስራቅ፤ ካታር አድርጓል። ሠዓሊ ተሰማ በኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገራቶች ተዟዙሮ ስራዎቹን ያቀረበ ሲሆን በዋናነትም በሰው ቁመት ልክ የሰራው የቡና ቅርጽ፤ በካታር የቅርስ ማዕከል በሚካሄድ ትዕይንት አካል በመሆን እስከ መጪው መጋቢት ድረስ ለዕይታ ክፍት ሆኗል። 

ቅርጹ በነሃስ በድጋሚ ተሰርቶ በካታር በተመረጠ ጎዳና ላይ እንዲቀመጥ እንቅስቃሴ መጀመሩንም አርቲስቱ ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል። “የሥዕል ስራዎቼ ደግነትን እና ሀገር ማስተዋወቅ እንዲሁም ዲፕሎማሲን ዓላማ ያደረጉ ናቸው” የሚለው አርቲስቱ፤ በዋናነት የሙሉ ጊዜ መተዳደሪያው የአቪዬሽን ስራ ነው። ሠዓሊ ተሰማ በቅርቡ የሥዕል ስቱዲዮውን ወደ ጋለሪነት ለማሳደግ ዓልሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ አጋርቷል።