የአእምሮ ጤና እና ስኬታማነት

Your browser doesn’t support HTML5

ፈጣን እና ተለዋዋጭ በኾነው ዓለም ውስጥ፣ ብዙ አዳጊዎች እና ወጣቶች፥ በትምህርት ጫና፣ በኑሮ ውድነት፣ በሥራ አጥነት፣ እንዲሁም በሌሎች መሰል ተግዳሮቶች ለስሜት ጫና ይዳረጋሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም፣ ብዙዎች፣ በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች፣ ይህን መሰል ጫናቸውን ሲያጋሩ ይስተዋላል።
ስኬታማ እና ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር፣ የአእምሮ ጤንነት እና የአስተሳሰብ ቀናነት፣ እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው።
በዚኽ ጉዳይ፣ የአሜሪካ ድምፅ፥ “የሶፊያ ሚዲያ እና የግሬትነስ ሾው” መሥራች፣ እንዲሁም የሕይወት
ክህሎት አሠልጣኝ ከኾነችው ሶፊያ አብዱልቃድር ጋራ ቆይታ አድርጓል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/