“ምዥዥጓ ሎካ” - እልፍ ሴቶችን ከአጉል ልማድ የታደገው የትርሃስ አሻራ

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን፣ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. “አካታችነትን ማነቃቃት” በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል፡፡  ዕለቱን በማሰብ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ሴቶች በወሊድ እና በወር አበባ ወቅት ወደ ጫካ እንዲገቡና እንዲገለሉ የሚገደዱበት አጉል ልማድ ሙሉ ለሙሉ እንዲቀር፣ ከሁለት ዐሥርት ዓመታት በላይ የሠራን ተቋም ጋብዟል፡፡ ተቋሙ “ምዥዥጓ ሎካ” ይባላል፡፡ አሁን በሕይወት በሌለችው ወጣት ትርሃስ መዝገበ አማካይነት የተመሠረተ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ በተጨማሪም፣ ልዩ ልዩ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚያርፉባቸውን ቤቶች በማዘጋጀት የጤና፣ የፍትሕ እና የሥነ ልቡና ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ የተሰናዳው ዘገባ ይቀጥላል፡፡