ዳያስፖራ እናቶች በዝግ የሚመካከሩበት “ሐበሻ ማምስ”

Your browser doesn’t support HTML5

ሐበሻ ማምስ፥ የዳያስፖራ እናቶች የፌስቡክ ቡድን ነው፡፡ በጎሮጎርሳውያኑ 2014፣ ነዋሪነቷን በሲያትል ዋሺንግተን ግዛት ባደረገች እናት የተመሠረተ ሲኾን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን እናቶች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በዝግ ይወያዩበታል፡፡

ቡድኑ በዓለም ዙሪያ፣ ከ15ሺሕ በላይ ዲያስፖራ እናቶች በአባልነት ሲኖሩት፣ በውጭው ዓለም ልጆችን ማሳደግ፣ ትዳር፣ ትምህርት፣ ጤና እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ አርእስተ ጉዳዮች ለውይይት ይቀርቡበታል። በተለያዩ ግዛቶች እና ሀገራት ያሉ እናቶችም በአካል ተገናኝተው እንዲወያዩም ለማድረግ ችሏል።

ኤደን ገረመው፣ የሐበሻ ማምስ ፌስቡክ ገጽንና የእህት ተቋሙ “አልማስ ኤንድ ኮ” መሥራቿን ቤሪ ገብረ ሕይወትንና ሌሎች የገጹ አባላት የኾኑ እናቶችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።