የሴቶች እና ህጻናትን ጥቃት በዘላቂነት ለመቅረፍ መፍትሄው ምን ይሆን?

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፉት ጥቂት ወራት የህጻናት ሴቶች በአስሰቃቂ ሁኔታ የአስገድዶ መደፈር ዜናዎች በተደጋጋሚ ሲሰሙ ሰንብተዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ተቋማትም በፍትህ አሰጠጣጥ ዙሪያ እንዲሁም ለችግሩ መንስዔ ሊሆኑ ይችላሉ በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሲሰጡ ሰንበተዋል።

ይኸን ተትሎም ኤደን ገረመው ለመሆኑ የሴቶች እና ህጻናትን ጥቃት ከስር ከመሰረቱ ለመቅረፍ ምን ሊደረግ ይገባል? ትላላቹ ሲል የከለላ የልጆች ወሲባዊ ጥቃት መከላከያ መርጃ መስራች ሰላማዊት ሙሴን እና በወጣት ሴት በጎ ፈቃደኞች እና የስርዓተ ጾታ ባለሞያዎች አማካኝነት ከሦስት ዓመታት በፊት የተጀመረው የድረ-ገጽ የመወያያ መድረክ አዲስ ፓወር ሀውስ መስራች ሀና ለማን አነጋግራለች።