ዓለም አቀፍ ታሪካዊ እና ሥነ ጥበባዊ ሥራዎችን የሚይዘው ሙዚየሙ፣ ከጥንታውያን ስብስቦች በተጨማሪ፣ የዘመነኛ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን የሥዕል እና የቅርጻቅርጽ ግብሮችንም አካቷል።
ኤደን ገረመው፣ በኢትዮጵያ መንፈሳዊ ሥዕሎች ላይ፣ ከ30 ዓመታት በላይ ምርምር ያደረገችውን ክርስቲን ሻካን፣ ዓለም አቀፍ የጥበብ ባለሞያን ጸደይ መኰንንና ሌሎችንም ባለሞያዎችን አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።