እንሰት ድርቅን በመቋቋምና ረዥም ጊዜ በመቀመጥ፣ እንዲሁም አስከፊ የአየር ንብረት ቀውስን በመቋቋም፣ "ልዕለ ምግብ" እየተሰኘ እስከ መጠራት ደርሷል።
ወጣቶቹ፣ ኢትዮጵያ ወደ ሀገር ውስጥ ከምታስገባው የዱቄት ገበያ፣ በትንሹ 20 በመቶውን የመጋራት ሕልም እንዳላቸውም፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። ኤደን ገረመው፣ ከመሥራቾቹ መካከል የኾነውን እሱባለው አለልኝን፣ ስለ ተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴ አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ይቀጥላል።