ለመሆኑ እነዚህ ወጣቶች ድምጻቸውን ለመስጠት መመዘኛቸው ምንድነው? በሎስ አንጀለስ ስቴትስ ዩኒቨስርቲ መምህርት የሆኑት የፖለቲካ ሳይንስ አዋቂዋ ዶ/ር ሳባ ተስፋዬ ዮሃንስን ጋብዘናል። ያነጋገረቻቸው ኤደን ገረመው ናት ። አስከትለን የምናልፈው ወደዛው ነው፡፡
ትወልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ጄን-ዚዎች ድምጻቸውን ለመስጠት መመዘኛቸው ምንድነው?
Your browser doesn’t support HTML5
የዩናይትድ ስቴትስ ህዝቦች 48ኛውን የሀገሪቱን ፕሬዚደንት ለመመምረጥ በተሰናዱበት ፣ በአንዳንድ ስፍራዎችም መምረጥ በጀመሩበት ወቅት ላይ እንገኛለን ። በመቶ ሚሊዮኖች ከሚቆጠሩት መራጮች መካከል ፣ ወጣቶችም በዚህ ፖለቲካዊ ሁነት ላይ ለመሳተፍ ተሰናድተዋል ። 41 ሚሊየን የሚደርሱ ከጎሮጎርሳዊያኑ 1997 በኋላ የተወልዱ ጄን ዚ መራጮች ያሉ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወጣቶች ይገኙበታል።