እንደ አረም ቢቆጠርም በሥነ ምግብ ይዘቱ የላቀው አማራንዝ

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራንዝ ግብርና ኢኮሎጂ የሲቪክ ማኅበረሰብ፣ በኢትዮጵያ፥ በቀላሉ የሚበቅሉ ሀገር በቀል ተክሎችን በመጠቀም፣ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናት፣ በይዘቱ የበለጸገ አልሚ ምግብ እንዲያገኙ ግንዛቤ በመፍጠር ላይ ይገኛል።
ተቋሙ ከተመሠረተ ሁለት ዓመታትን ሲያስቆጥር፣ በዐዲስ አበባ ከተማ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የሥነ ምግብ ጠቀሜታ ያላቸው ምግቦች በኅብረተሰቡ ዘንድ እንዲለመዱ ለማድረግ እየጣረ እንደኾነ፣ የተቋሙ መሥራች እና ዲሬክተር ወ/ሮ ሙሉነሽ ጀቤሳ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
በተለይም፣ በብዙ የአገሪቱ ክፍሎች የሚበቅሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ዕፀዋት እና አዝርዕት መኖራቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ ሙሉነሽ፣ እነዚኽን ለማኅበረሰቡ በማስተዋወቅ ላይ እንደሚሠሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም ሲቪክ ማኅበሩ፣ በግብርና ዙሪያ የተሠሩ የተለያዩ የመመረቂያ ጥናቶች ተግባራዊ እንዲኾኑ እንደሚጥርም አክለዋል።