ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ድጋፍ የሚሰጠው ተቋም

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እና ወጣቶች የአመራር ክህሎት እንዲኖራቸው፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን፣ የኮምፒውተር ክህሎታቸውንና ችግር ፈቺ የኾነ አስተሳሰባቸውን እንዲያዳብሩ 'ብራይተር ጄኔሬሽን' ወይም ‘ብሩህ ትውልድ’  የተሰኘው በዩናይትድ ስቴትስ የተመሰረት፤ ተቋም በማገዝ ላይ ይገኛል።

ተቋሙ ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኞችን በአስር ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የተቋሙ ማዕከላት ጋራ በማቆራኘት ሥልጠናዎችን እየሰጠ ነው። ተቋሙን የመሰረቱት በዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር ምርምር ድርጅት (ናሳ) ተመራማሪ ዶክተር ብርሃኑ ቡልቻና ባለቤታቸው የሥነሕይወት ኬሚስትሪ ተመራማሪ ዶ/ር ጸጋ እንዲሁምናቸው። ኤደን ገረመው የተቋሙን መስራቾች፣ በጎፈቃደኞችንና የመርሃግብሩ ተሳታፊዎች አነጋግራ ያሰናዳችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።