የአካላዊ እና የስነልቦና ጥቃት ሰለባዎችን በዳንስ ማከም

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ አፍሪካዊው መምህር፣ ለጥቃት የተጋለጡ አዳጊዎችን በዳንስ ቡድን ያበረታታል። መምህሩ፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ በትምህርት ቤት ውስጥ የመንጓጠጥ እና የማበጥ ሞራላዊ እና አካላዊ ጥቃት ይደርስበት እንደነበር ያስታውሳል። አሁን፣ "ሕብረ ኬፕታውን"(Colorful Capetown) በተሰኘው ትዕይንተ ሕዝብ ላይ የአዳጊ ዳንስ ቡድኑን ይዞ ተሳትፏል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት ፈንድ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙ ደቡብ አፍሪካውያን ማኅበረሰቦች ዘንድ፣ "ቡሊ" የተሰኘው የማበጥ ችግር የተስፋፋ መኾኑንና እስከ አዋቂነት ዕድሜ የሚዘልቁ ጉዳቶችም እንዳሉት አመላክቷል። ዘገባው የቪኪ ስታርክ ነው ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።