በዐማርኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ተግባቦት መረጃዎችን የሚያደራጀው ሰው ሠራሽ አእምሮ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማርኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች ተግባቦት መረጃዎችን በማሰናሰል፣ በተፈለገው ርእሰ ጉዳይ፣ የተለያዩ ዝርዝር ጽሑፎችን ያደራጃል፡፡በተጨማሪም፣ በፖለቲካ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች፣ ማኅበረሰብ ተኮር መረጃዎችን ያቀርባል፡፡

ከቴክኖሎጂው መሥራቾቹ አንዷ የኾነችውን ሩት ብርሃነ፣ ሰው ሰው ሠራሹ አእምሮ(AI)፣ በሰው ልጆች ላይ የደቀነውን፣ የሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ስጋት በመገንዘብ፣ ሰው ሠራሹ አእምሮ(AI) በመረጃዎች ላይ የተደረጉ ነገሮችን ብቻ እንዲያጋራ ኾኖ መዘጋጀቱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጻለች፡፡