ድባቴ እና እራስን ማጥፋት

Your browser doesn’t support HTML5

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ በተለያዩ ምክንያቶች እራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች ዜና መስማት እየተደጋገመ ሄዷል። ምንም እንኳን ሰዎች እራሳቸውን የሚያጠፉባቸው ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም በዋናነት ግን ተስፋ መቁረጥ እና ድባቴ እንደ ምክንያት ይነሳሉ።

አጠቃላይ የጤና ሃኪም እና የስነ አዕምሮ ህክምና እጩ ሃኪም ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው በድባቴ እና እራስን ማጥፋት ዙሪያ ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ምንም እንኳን በአዕምሮ ጤና ዙሪያ የግንዛቤ እጥረት ቢኖርም በከተሞች ባሉ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ውስጥ ግን የማማከር አገግሎት ለመስጠት ተብለው የተከፈቱ ቢሮዎች እና የተቀመጡ ባለሞያዎች መኖራቸውን ይገልጻሉ። ድባቴ፣ ተስፋ መቁረጥ እና እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ህክምናውን ሊያገኙ እሚችሉባቸው የተሻሉ አማጮች መቅረባቸውንም ጠቁመዋል።

/ ሙሉ ቆይታውን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/