የ"አራዳ ቋንቋ" ስነዳ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ከእኩዮቻቸው ጋር በሚስጥራዊ መንገድ ለመግባባት ፣ ለሹፈት እና ለጨዋታ ሲሉ የተለያዩ ከመደበኛ የቃላት አጠቃቀም ስርዓት ዘወርወር ያሉ ቃላቶችን በየጊዜው ይፈጥራሉ፡፡ እነዚህን አዳዲስ ቃላቶች የሚያስተናግደው ኢ-መደበኛ ዘዬ ታዲያ በተለምዶ የ"አራዳ ቋንቋ" ይሰኛል፡፡

ጋቢና ቪኦኤ በዚህ መሰናዶ የዚህን ዘመን "የአራዳ ቃላቶች " ሰፊው ህብረተሰብም ያውቅ ዘንድ በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ በመሰነድ ላይ የምትገኘውን ወጣት ሕይወት አበበን ያስተዋውቃችኃል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው የስነ-ልሳን ትምህርት ክፍል መምህር ፕሮፌሰር ዘላለም ልየው ደግሞ የአራዳ ቋንቋን ይዘት እና ባህሪያት ያስረዱናል።

/ሙሉ ዘገባውን ከተያይዘው ፋይል ይከታተሉ/