ከፍልሰት ተመላሽ ወጣት ኢትዮጵያውያን የጉዞ ሠቆቃቸውን ያጋራሉ
በየዓመቱ፣ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፣ የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እና የአውሮፓ ሀገራት ይፈልሳሉ። ወጣቶቹ፣ ሕገ ወጥ መንገዶችን የሚጠቀሙ ሲኾን፣ ሕይወታቸውን እስከማጣት ለሚያደርስ አደጋ ይጋለጣሉ። ሰሞኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ከፍልሰት ተመላሾች መጠለያ ተገኝቶ፣ ወጣቶቹን፣ በጉዟቸው ስላጋጠሟቸው አሠቃቂ ጉዳዮች አነጋግሯቸዋል። የኤ.ኤፍ.ፒን ዘገባ ኤደን ገረመው እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።