ኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅ ምክንያት የሚፈናቀለው ሰውና የሚሞተው እንስሣ እየበዛ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅ ምክንያት 175 ሺህ ሰው መፈናቀሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። በውኃና መኖ መጥፋት ምክንያት ከአንድ ሚሊየን ተኩል በላይ ከብቶችና ሌሎችም እንስሣት ማለቃቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች ገልፀዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ጥረቱን ማጠናከሩንና ሁለት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ ለሚሆኑ ተጎጂዎች የምግብ እርዳታ ማድረሱንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ተጨማሪ ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።