ኦቲዝም እና መደረግ ያለባቸው ድጋፎች

Your browser doesn’t support HTML5

ኦቲዝም የአንጎልና የነርቭ ሥርዐት ውስንነት ሲኾን፤ በዓለም ላይ ከ100 ህጻናት አንዱ ይህ ውስንነት እንደሚያጋጥመው የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል። አብዛኛውን ጊዜም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ዓይን ለዓይን የመተያየት፣ የማኅበራዊ መስተጋብር እና ተግባቦት ላይ እክል ያጋጥማቸዋል።ስለ ኦቲዝም በቂ መረጃ እና ምርመራ በሌለበት የአፍሪካ ሃገራት ላይ ችግር ደቅኗል። በግንዛቤ እጥረት እና መገለልን በመፍራት ወላጆች የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ልጆቻቸውን አስፈላጊ ድጋፍ እንዲያገኙ እንደማያደርጉ ባለሞያዎች ይናገራሉ።