የደም ግፊት መጠን ለምን ይጨምራል?

Your browser doesn’t support HTML5

ሃይፐር ቴንሽን ወይም የደም ግፊት መጠን መጨመር በደም ስሮች ውስጥ የሚዘዋወረው የደም ፍሰት ግፊት ሲጨምር ይከሰታል፡፡ የደም ግፊት መጠን፤ ደም፤ ደም ቀጂ ተብሎ ከሚታወቀው የልብ ደም ማስተላለፊያ የሚረጭበትን የጉልበት መጠን በመለካት የሚታወቅ ነው፡፡

የአለም የጤና ድርጅት ጤናማ የሚባለው የደም መጠን 120/80 እና ከዛ ያነሰ ነው ሲል ያስቀምጣል፡፡ አንድ ሰው የደም ግፊት መጠኑ ከፍተኛ ነው የሚባለው 140/90 እና ከዛ በላይ ሲሆን ነው፡፡ የደም ግፊት መጠን መጨመር ምልክት የማያሳይ በመሆኑ ለድንገተኛ የልብ ህመም እና ደም ወደ ጭንቅላት መድረስ ሲያቅተው የሚፈጠር እራስን መሳት ያስከትላል፡፡ የደም ግፊት መጠን መጨመር በዓለም ዙሪያ ከአንድ ቢሊየን በላይ ሰዎች የጤና ችግር መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት በቅርቡ አስታውቋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የኑሮ በጤንነት መሰናዶ ይከታተሉ/