በወጣቶች ላይ የሚከሰት የሰውነት አለመታዘዝ እና የነርቮች ጉዳት

Your browser doesn’t support HTML5

በእንግሊዘኛ አጠራሩ ስትሮክ ወይም የሰውነት አለመታዘዝ በአዕምሮ ውስጥ የሚኖረው የደም ዝውውር ሲገደብ እና የደም ስሮቻቸን ሲበጠሱ የሚከሰት ነው። በጎልማሶች ላይ የሚከሰት ስትሮክ የተለመደ ሲሆን አሁን አሁን ግን ወጣቶችም ላይ እየጨመረ መሄዱን ባለሞያዎች ይናገራሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል ሲዲሲ አዋቂዎች እድሜያቸው ከ55 ዓመት ካለፋቸው በኋላ በየአስር ዓመቱ በስትሮክ የመጎዳት እድላቸው ከቀድሞው በእጥፍ እንደሚጨምር አመላክቷል።

ለስትሮክ በምክንያትነት ከሚነሱ ነገሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት፣ ስኳር እና ቅጥ ያጣ ውፍረት ተጠቃሾቹ ናቸው። በዚህ ዙሪያ የተሰናዳውን ዘገባ ይከታተሉ።