የአጥንት ብግነት አርተራይተስ

Your browser doesn’t support HTML5

አርተራይተስ ወይም የአጥንት ብግነት መገጣጠሚያ ላይ የሚከሰት እብጠት፣ የአጥንት ድርቅ ብሎ የመሰማት ስሜት፣ የእንቅስቃሴ ማዳገት ምልክቶቹ ሲሆኑ፤ በአለም ላይ ብዙዎችን ለህመም ብሎም ለአካል ጉዳት የዳረገ በሽታ ነው። ከመቶ በላይ የአጥንት ብግነት ዓይነቶች ሲኖሩ ከሁሉም ልቆ የሚታወቀው በእንግሊዘኛው ኦስቴዮ አርተራይተስ ተብሎ የሚጠራው ዓይነት ነው።

እስከ ጎርጎርሳውያኑ 2019 ባለው ጊዜ በአለም ዙሪያ 528 ሚሊየን ሰዎች በበሽታው መጠቃታቸውን የአለም የጤና ድርጅት መረጃዎች ያመላክታሉ።