ለታዳጊ እናቶች ተሰፋ የሆነው ጣሊታ ተቋም
Your browser doesn’t support HTML5
ጣሊታ ራይዝ አፕ ከተመሰረተ 12 ዓመታትን ያስቆጠረ ተቋም ሲሆን በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን እና እንጦጦ አካባቢ እንዲሁም በሲዳማ ክልል ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ሴቶችን በማኖር፣ ፍትህ እንዲያገኙ በመታገል፣ በጾታዊ ጥቃት በተፈጠሩ እርግዝናዎች የተወለዱ ልጆችን በማሳደግ እየረዳ ይገኛል፡፡ ተቋሙ ለመመስረቱ በዋንናነት መስራቿ ወ/ሮ አትክልት ጃንካ በልጅነታቸው ችግርን ለማምለጥ ብለው ተታለው የገቡበት ትዳር መነሻ እንደሆናቸው ይናገራሉ፡፡