በግለሰብ ጥረት የተቋቋመው ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ

Your browser doesn’t support HTML5

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል ከአራት ዓመታት በፊት በጥላሁን ማሞ የተመሰረተ ቤተመጽሃፍት ነው። ጥላሁን ከነበረው የማንበብ ፍቅር በመነሳት ያለውን ለማጋራት እንደወሰነ ይናገራል። ልህቀት ባለፉት ዓመታትም ከበጎ ፍቃደኞች ጋር በመሆን ማንኛውም ሰው ሊጠቀምበት የሚችል የንባብ ስፍራ መሆን ችሏአል። በተጨማሪም ደግሞ የተለያዩ የመጽሃፍ ሂስዎች እና ውይይት የሚደረጉበት እንዲሁም በክረምት ወራት ወጣቶች ለንባብ የሚሰባሰቡበት ስፍራ መሆን እንደቻለም ጥላሁን ይናገራል።

ማዕከሉ በቅርቡ ሁለተኛ ቅርጫፍ ከፍቷል። ስለ ቤተመጽሃፉ አመሰራረት እና እየሰሩት ስላለው ስራ፣ የቤተ መጽሃፍቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆነው ጥላሁን ማሞ እና ተገልጋዮች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ያግኙ/