በድባቴ እና እራስን በማጥፋት ስሜት ውስጥ ያሉ ወጣቶች ስለአዕምሮ ጤና የሚወያዩበት ቡድን  

Your browser doesn’t support HTML5

እኛ ለእኛ የወጣቶች የአዕምሮ ጤና የመወያያ ቡድን ከአንድ ዓመት በፊት በወጣት አዲስ ተቻል እና ጓደኞቿ የተመሰረተ ነው። አዲስ ቡድኑን ከመመስረቷ በፊት ከፍተኛ በሆነ የመንፈስ ጭንቀት እና ሱስ ለሰባት ዓመታት ያህል መሰቃየቷን ትናገራለች። አዲስ ከሦስት ጊዜ በላይ እራሷን ለማጥፋት ሞክራ እንደነበርም ትናገራለች።

በህክምና ይበልጡን ደግሞ በመንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ባሉ ወዳጆቿ ድጋፍ ከነበረችበት የአዕምሮ ጤና ችግር ከወጣች በኋላም በዚህ ስሜት ውስጥ ያሉ ወጣቶች በሳምንት አንዴ በአካል እንዲሁም በድረ ገጽ ተገናኝተው ስለሚሰሟቸው ስሜቶች የሚማከሩበት ቡድን ልትመሰርት ችላለች።

/አዲስ ተቻል ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ከተያያዘው የምስል ፋይል ያግኙ/