በስዕል ውስጥ እራሷን ያገኘችው ሰላማዊት ገብረጻዲቅ

Your browser doesn’t support HTML5

ሰላማዊት ገብረጻዲቅ የስዕል ጥበብን ከመማሯ በፊት፤ ሕግ ፤ ቀጥሎ ደግሞ አካውንቲንግ ተምራለች። ኑሮን ለመግፋት የያዘችው ስራ ግን ደስታን ነፍጓት ቆይቷል ትላለች። ቅጠሎችን በመጠቀም በምትሰራቸው ስዕሎች እውቅና ማግኘት ችላለች። አብዛኞቹ ስዕሎቿም ሰብዓዊ መብት የሴቶች እና ሕጻናትን መከራ እንዲሁም የሰው ልጅ ከአካባቢው ጋር ያለውን ቁርኝት የሚያስቃኙ ናቸው። ሰላማዊት ከአሜሪካ ድምጽ ጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርጋለች። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/