ፕላቲነም የተሰኘ ጥንታዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያ ረድኤት ወንድሙ

Your browser doesn’t support HTML5

ፕላቲነም የተሰኘ ጥንታዊ የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያ ረድኤት ወንድሙ አስመራ ተወልዳ ኢትዮጵያ ያደገችው ረድኤት ወንድሙ በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ሳለች ከሰባት እህትና ወንድሞቿ ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመሄድ በቺካጎ ግዛት አድጋለች። የፎቶግራፍ ጥበብ የልጅነት ህልሟ ቢሆንም በዙሪያዋ ባሉ ሰዎች ጫና ነርሲንግ ተምራለች። ይሁን እንጂ በዛ ሙ ያ ላይ ከዚህ በላይ ለመቆየት እንዳልፈለገች በመግለጽ ከጊዜ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ፊቴን ወደ ፎቶግራፍ ጥበብ አዞርኩ ትላለች።