በመጪው የትምህርት ዘመን ለሴቶች የንጽሕና መጠበቂያዎች ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

“ዓደይ ፓድስ”፥ በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ፣ የወር አበባ እና የፈሳሽ መቆጣጠሪያ የንጽሕና መጠበቂያዎችን፣ ለሴቶች እና ለልጃገረዶች የሚያቀርብ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ፣ በንጽሕና መጠበቂያ ጥቅሎች እጥረት ምክንያት፣ ከትምህርታቸው ለሚስተጓጎሉ ልጃገረዶች፣ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የንጽሕና መጠበቂያ ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም፣ ለብዙ ሴቶች የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ችሏል፡፡

የተቋሙ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚካል ማሞ፣ የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ጥቅልን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ፣ በጉዳዩ ላይ ከሚሠሩ ልዩ ልዩ ተቋማት ጋራ እየሠሩ እንደኾነ ገልጻለች፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አያይዛም፣ በዐዲሱ የትምህርት ዘመን፣ ከትምህርት ቁሳቁሶች ጋራ፣ የንጽሕና መጠበቂያዎችም ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስባለች፡፡