ወንዶች ያርጣሉ?
Your browser doesn’t support HTML5
ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት ያለፈና በተለይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማያደርጉ ወንዶች፣ ቴስቴስትሮን የተሰኘው የወንድ ጾታ ሆርሞን መቀነስ እንደሚያጋጥማቸውና ሊያርጡ እንደሚችሉ፣ እ.አ.አ. በ2018 በዩናይትድ ስቴትስ የታተመው “የቤተሰብ እና የሥነ ተዋልዶ ጤና” መጽሔት ይጠቁማል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኩላሊት፣ የሽንት ቱቦ እና የፕሮስቴት ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ሀብታሙ አደራው፣ በጉዳዩ ላይ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡፡