የ“ኢትዮ ጃዝ” ዘላቂነት ለወጣቱ ትውልድ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮ ጃዝ፣ የኢትዮጵያ ሙዚቃ “ወርቃማ ዓመታት” የተሰኙትን የ1960 እና 1970ዎቹን ሙዚቃዎች ለመዘከር፣ ባለፉት አራት ዓመታት፣ በዐዲስ አበባ ተከታታይ ዐውደ ትርኢቶችን (ፌስቲቫሎችን) ሲያካሒድ ቆይቷል። ይኸው ዐውደ ትርኢት፣ ከዓመት እስከ ዓመት ሞቅ ደመቅ እያለ መቀጠል ችሏል። ኢትዮጵያዊ መልክእ ያለው “ኢትዮ ጃዝ” የተሰኘው የጃዝ ሙዚቃ ስልት፣ በዓለም ላይ ተወዳጅ እንደኾነም ይነገርለታል።
የጃዝ ሙዚቃ ስልቱ፥ በ1950 ዓ.ም. በአርመኔያዊው የሙዚቃ ባለሞያ በሙሴ ነርሲስ ናልባንዲያን አማካይነት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃን፣ ከዘመናዊው ሙዚቃ እና የጃዝ ስልት ጋራ በማጣመር የተጀመረ ነው። ይህም አገሪቱ፣ ልዩ የኾነ የራሷ የጃዝ ሙዚቃ ቃና እንዲኖራት አስችሏታል።
በፌስቲቫሉ ላይ የሚሳተፉ ልዩ ልዩ የሙዚቃ ባለሞያዎች፥ እኒያን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዓመታት በማስታወስ፣ “የኢትዮጵያ ያልተነካ ዕሤት” የኾነውን የኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ስልት፣ በወጣቱ ትውልድ ዘንድ በሚገባ እንዲዘልቅና እንዲሠራበት ይመክራሉ።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/