በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሴቶች ሳይክል እንዲነዱ የወጠነው ‘ሳይክል ትችያለሽ’ መርሃግብር  

Your browser doesn’t support HTML5

አዲስ አበባ ላይ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት በጥቂት ወጣቶች የተጀመረው፤ እሁድ ጠዋትን ሳይክል በመጋለብ የማሳለፍ ባህል እየሰፋ መጥቷል። እግረመንገድ የተሰኘው የሳይክል ማኅበረሰብ ከመቶ በላይ ወጣቶችን የሚያሳተፍ ቢሆን ከዚህ ውስጥ ግን ከሶስት የማይበልጡ ሴቶች ብቻ እንደነበሩ የቡድኑ አጋር መስራች ኤፍሬም በቀለ ይናገራል።  

ይህንን ችግር ለመቅረፍም ከለም ከተማ ተቋም በመተባበር ለሁለት ወራት ያህል 16 ሴቶችን ‘ሳይክል ትችያለሽ’ በተሰኘ መርሃግብር በመተባበር አሰልጥነው አስመርቀዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/