ቻይና የኢትዮጵያ ምርቶች ያለ ቀረጥ እንዲገቡ ፈቅዳለች

Your browser doesn’t support HTML5

የንግድና ምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች አስተያየት ሰጥተውበታል ቻይና ከ1ሺ በላይ የተለያዩ የኢትዮጵያ ምርቶች ያለ ቀረጥ እንዲገቡ መፍቀዷ ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን ከዝርዝሩ ውጭ ባደረገችበት የአፍሪካ የዕድገትና የዕድሎች ተጠቃሚነት ህግ /አገዋ/ ዕድል ሊያካክስ እንደሚችል የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎቹ ዶ/ር አረጋ ሹመቴና ዶ/ር ፈቃደ ገላዬ ለቪኦኤ ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ አቶ ውቤ መንግሥቱ ደግሞ ‘እስከዛሬ አምልጠዋል’ ያሏቸውን ተመሳሳይ ዕድሎች በመጠቅስ የአሁኑ ዕድል ጥቅም ሊኖረው እንደሚችል አመክተዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/