“አዲስ አበባ ውስጥ በህዝብ ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂው የከተማዪቱ አስተዳደር ነው” እንባ ጠባቂ

Your browser doesn’t support HTML5

በአንዳንድ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማን ለመስቀልም ሆነ መዝሙር ለማስዘመር በሚደረግ እንቅስቃሴ በተማሪዎችና በህዝብ ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተጠያቂው የከተማዪቱ አስተዳደር ነው” ሲል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም አስታውቋል። ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀልም ሆነ መዝሙር ለማስዘመር ህጋዊ አካሄዶችን መከተል እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

ከቀናት በፊት ከአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎች ጋር የተወያዩት ከንቲባ አዳነች አበቤ “ችግሮች እንዲባባሱ የሚያደርጉት በግጭት የሚያተርፉ አካላት ናቸው” ብለዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/