በእሥልምናው ዓለም ውስጥ ሰሞኑን የሚታየው ሁከት የዓለምን ቀልብ ይዟል፡፡በእሥልምናው ዓለም ውስጥ ሰሞኑን የሚታየው ሁከት የዓለምን ቀልብ ይዟል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
በዚህ ሣምንት ውስጥ ሊብያ እና ግብፅ ውስጥ የተከሰቱት አመፆች ምንም ያህል ስሜትን የሚነካ ቢሆን ሃሣብን በነፃነት በመግለፃ ነፃነት እና በእምነት ክብር መካከል ያለውን የቆዩ ግጭቶችና ፍጭቶች ወደአደባባይ አውጥቷቸዋል፡
የግብፅ ቴሌቪዥን ከእንግሊዝኛ ወደ አረብኛ ተርጉሞ ያሣየው “መደዴ” ቪድዮ ነው የሁከቱ ሁሉ መንስዔ፡
ሊብያ ውስጥ የአሜሪካ አምባሣደርና ሌሎች ሦስት የኤምባሲው ባልደረቦች አደባባይ ወጥተው ሁከት ባስነሱ ሊብያዊያን ተገድለዋል፡፡ ኤምባሲው ወድሟል፤ ተቃጥሏል፡፡
በካይሮ የአሜሪካ ኤምባሲ ብዙ ሁከት ደርሶበታል፤ ቅጥር ግቢው ሠልፈኞች ተደፍሯል፤ የአሜሪካ ባንዲራን አውርደው ተቀዳድደዋል፤ አቃጥለዋል፡፡ በሥፍራውም ጥቁር ባንዲራ ሠቅለዋል፡፡
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ፖሊሶች ወደዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ይጓዙ ከነበሩ በጀርመን ኤምባሲ ላይ ቃጠሎ ካደረሱና የእንግሊዝ ኤምባሲንም ከደፈሩ በሺዎች የተቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፈኞች ጋር ተጋጭተዋል። አስለቃሽ ጋዝ ረጭተውባቸዋል፡፡ በሁከቱ መካከል የሦስት ሰው ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡
በየመን ዋና ከተማ ሰንዓና በሌሎችም እሥልምና የመንግሥቱ ሃይማኖት በሆነባቸው ሃገሮች ውስጥ ተመሣሣይ ሁከቶች ደርሰዋል፡
የማንም ሰው ሃሣብን የመግለፅ እና የእምነት ነፃነቶች ዩናይትድ ስቴትስ ስትፈጠር ጀምሮ አብረው ያሉ፣ በሕገመንግሥቷም የተረጋገጡና የሕግ ጥበቃም የሚደረግላቸው ነፃነቶች መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ሂላሪ ክሊንተንን ጨምሮ የአሜሪካ ባለሥልጣናት አመልክተው አሜሪካ ውስጥ የፊልም ሥራ ሞያ በሌላቸው ሰዎች በቤት ውስጥና በአነስተኛ ገቢ የተሠራው የነቢዩ መሐመድን እና የእሥልምናን ክብር ይነካል የተባለውን ፊልም ይዘት እንደማይደግፉትና እንደሚያወግዙትም መንግሥታቸውም ስለፊልሙ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልፀዋል፡
ይሁን እንጂ በሊብያና በሌሎችም ሃገሮች እየተፈፀሙ ያሉት የአመፃና የሁከት አድራጎቶች በምንም መንገድ ሊደገፉ እንደማይችሉም አረጋግጠዋል፡
ዩናይትድ ስቴትስ በየሃገሮቹ ያሏትን ኤምባሲዎቿን ደህንነት ለማረጋገጥ ጠበቃው እንዲጠናከር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አዘዋል፡፡ ሁከት ወደበዛባቸው ሃገሮችም ባሕር ወለድ ጦሯና መርከቦቿ እየተንቀሣቀሱ ነው፡፡
አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ለእንዲህ ዓይነቱ ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ችግር ጉዳይ መድኃኒቱ የበለጠና የሰፋ ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ነው፡
ካይሮ የምትገኘው ኤሊዛቤጥ አሮት አንዳንዶቹን አነጋግራ የላከችው ዘገባ አለ፤ ያዳምጡት፡፡