ድምጽ ትውልደ ኢትዮጵያና ኤርትራውያን በቬጋስ ተሰለፉ ማርች 18, 2021 Your browser doesn’t support HTML5 ትንናት ረቡዕ በኔቫዳ ክፍለ ግዛት ላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ የሚገኙ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን፣ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ፣ የአሜሪካና የውጭ አገር መንግሥታት፣ በኢትዮጵያው የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና አድሏዊነት፣ ሁኔታውንም አስመልከቶ፣ የሚሰራጩት የሀሰት ዘመቻዎችም እንዲቆሙ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል፡፡