በካሜሩን የሚገኙ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ፣ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ እዚያ ሆነው በአገሪቱ ከተገንጣዮች ጋር የተፈጠረውን ግጭት በማባባስ፣ ነውጥና ብጥብጥን የሚያቀጣጥሉ ናቸው ብለዋቸዋል፡፡ የካሜሩን መንግሥት መገናኛ ብዙሃንም ውሳኔውን በጥሩ ጎኑ እያቀረቡት ነው፡፡ የቪኦኤ ሪፖርተር፣ ሞኪ ኤድዊን ካይንድዜካ፣ ከዱዋላ የሚከተለውን ዘገባ ልኳል፡፡
ወደ 20 የሚጠጉ ካሜሩናውያን ትናንት ረቡዕ በዱዋላ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተሰብሰበዋል፡፡ ከዩናይትድ ስቴትስ ተባረው የሚመጡ ዘመዶቻቸውን እየተጠባበቁ ነው፡፡ የ27 ዓመቷ ጄኒፈር ሞኔ ታላቅ ወንድሟ ወደ ካሜሩን ተመልሶ የሚመጣ ከሆነ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል በማሰብ ሰግታለች፡፡ ወንድሟ ከካሜሩን ለመገንጠል የሚፈልጉት የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች የፈጠሩትን ግጭት በመሸሽ ነበር ባለፈው ዓመት አገር ጥሎ የወጣው፡፡ እንዲህ ትላለች ሞኔ
ሞኔ እንደምትለው እሷንና ወንድሟን የሚቀበል ሌላ አገር እያፈላለገች ነው፡፡ የካሜሩን መንግሥት ስደተኞችን ከዩናይትድ ስቴት ስ መባረር ወይም ተመልሶ መምጣት አላረጋገጠም፡፡ የካሜሩን ሬድዮ ቴሊቪዝኝ ግን 120 የሚሆኑ ስደተኞቹ ትናንት ረቡዕ ከዳላስ ቴክሳስ መሳፈራቸውን ተናግሯል፡፡ ከዚያ ውስጥ 86 የሚሆኑት ካሜሩናውያን ሲሆኑ የተቀሩት ከዲሞክራቲክ ኮንጎ መሆናቸውንም ዘግቧል፡፡ ባለፈው ነሀሴ መንግሥት መራሹ የተቃውሞ ሰልፍ በካሜሩን ዋና ከተማ ያውንዴ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት የተካሄደ ሲሆን ዋሽንግተን አማጽያንን የሚደግፉ ካሜሩናውያንን ከአገራቸው ከስ እንዲመሰርትባቸው ወይም ከአገር እንዲባረሩ ጠይቀዋል፡፡ በሰልፉ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል፣ አክቲቪስት ሂልዳ ማኛ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ የተባረሩት ስደተኞች፣ተገንጣዮችን ደግፈው ከሆነ መመርመርና መቀጣት ይኖርባቸዋል በማለት እንዲህ ትላለች
የካሜሩን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ወደ አገራቸው ተባረው የተመለሱት ካሜሩናውያን መች ሊያዙ እንደሚችሉ ፍንጭ ባይሰጥም ሁኔታው በጣም ጥሩ መሆኑን እየገለጸ ነው፡፡ እንዲያውም ተመላሾቹ ዜጎች ካሜሩንን መልሶ ለመንገባት አስፈላጊዎች መሆናቸውን ገልጾ ባለሥልጣናቱ ስደተኞቹ ስደት ላይ ባሉበት ጊዜም ሆነ ከተመለሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን የጤና እንክብካቤ የሚሰጧቸውን የህክምና ባለሙያዎች የላኩላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አሌክዛንድራ ላማርቼ በመካከለኛና ምዕራብ አፍሪካ ከዓለም አቀፍ ስደተኞች ጋር የሚሰሩ ሲሆን ስደተኞቹን ወደ አገራቸው መልሶ የማባረሩ ሁኔታ አስደንጋጭ ነው ይላሉ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የስደተኞችና የቀረጥ አስፈጻሚው ኃይል ከአገር እንዲባረሩ በተወሰነባቸው ስደተኞች ጉዳይ ላይ ውሳኔው ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስ ምንም ዓይነት መግለጫ አለመስጠትን እንደ ፖሊሲ የሚይዘው ነው፡፡ ካሜሩናውያኑ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የገቡት ባለፈው አመት ሲሆን በደቡብ አሜሪካ አቆራርጠው በሜክሲኮ በኩል አድርገው ነው፡፡ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር ለጥገኝነት ጠያቂዎችና የህገወጥ ስደተኞች ሁኔታዎችን ጥብቅና አስቸጋሪ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በካሜሩንም ግጭት የተጀመረው በ2016 ነው፡፡ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ከሆነችው ካሜሩን ተገንጥለው ለመውጣት የሚሞክሩን እንግሊዚኛ ተናጋሪዎችን ፣ የካሜሩን ጦር ሰብሮ በመግባት ጥቃት ያደረሰባቸው በመሆኑ ነው፡፡ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎቹ ካሜሩናውያን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚታዩና ከመንግሥት ሥራም ሆነ ድጋፍ የማያገኙ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው የመገንጠሉ እንቅስቃሴ በፈጠረው ግጭት ከሶስት ሺ ሰዎች በላይ ሲሞቱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑን ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5